በስራ ቦታ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት 5 ጠቃሚ ምክሮች

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሚኖሩ አካ የተባለ ጎሳ አባላት የሆኑ ወንዶች ትንንሽ ልጆችን የመንከባከብ ሃላፊነት ያለባቸው ሲሆን ሴቶቹ ደግሞ ወደጫካ ሄደው የማደንና ምግብ የመሰብሰብ ተግባር ይፈጽማሉ። አባቶች ቤት ማጽዳት፣ ከልጆች ጋር መጫወት እና ምግብ የመመገብ ሥራ ሲሰሩ ነው የሚውሉት።

በዚህ ተግባራቸውም የዓለም ህዝብ ከእነዚህ ሰዎች ብዙ የምንማረው ነገረ አለ በማለት አድናቆት ሲያጎርፍላቸው ቆይቷል። ጥሩ አባትነት ከብዙ ዓመታት በኋላ ትርጓሜው እየተቀየረ የመጣ ይመስላል። በአሁኑ ሰዓት ስለልጆቻቸው ስሜት የሚጨነቁና በተሻለ መልኩ ከልጆቻቸው ጋር ጊዜ የሚያሳልፉ አባቶች እንደ ጥሩና አስተዋይ አባት ይታያሉ። በአጠቃላይ በሚባል ደረጃ እስከ ጎርጎሳውያኑ 1970ዎቹ ድረስ ከህጻናት ጋር በተያያዘ ስለአባቶች ሃላፊነት ብዙም እውቀት አልነበረም። ዋነኛውና ብዙ ጊዜ ብቸኛው ሃላፊነታቸው ኦኮኖሚያዊ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ነበር። በአምስተርዳም ቭሪጅ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ማሪያን ቤከርማንስ በሰሩት ተከታታይ ጥናት መሰረት ምንም እንኳን አንድ ልጅ ሁለት ቤተሰቦች ቢኖሩትም 99 በመቶ የሚሆነው የልጆች ሃላፊነት የሚሸፈነው በሴቶች (እናቶች) ነው። ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከአባቶቻቸው ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት ኖሯቸው ልጅነታቸውን ያሳለፉ ህጻናት የተሻለ የአእምሮ እድገትና ጥሩ ባህሪ ይታይባቸዋል። በህይወታቸውም ደስተኛ የመሆናቸው እድል ከፍ ያለ ሲሆን ከሌሎች ህጻናት ጋር ያላቸው ግንኙነትም ጥሩ ነው። በሌላ በኩል ከአባቶቻቸው እምብዛም ፍቅር ማግኘት ያልቻሉት ህጻናት ግን ብዙ የሥነ አእምሮ ችግሮች ይስተዋሉባቸዋል። ቀን ሥራ ውለው ማታ ላይ ወደቤት የሚመለሱ አባቶች ሁሌም ቢሆን ከልጆቻቸው ጋር መጫወት ይፈልጋሉ። በዚህ ሰዓት አባትና ልጅ የማይረሱ የጨዋታ ጊዜዎችን ማሳለፍ ይችላሉ። ድብብቆሽና አባሮሽ እንዲሁም ሌሎች ጨዋታዎችንም ያዘወትራሉ።

አብዛኛውን የቀኑን ጊዜ ቤት ውስጥ ከልጆች ጋር የሚያሳልፉት እናቶች ደግሞ ከልጆቻቸው ጋር ረጋ ያለና በመርህ ላይ የተመሰረት ግንኙነት ለመመስረት ይሞክራሉ። በተጨማሪም ምግብ መመገብ እንዲሁም ንጽህናቸውን መጠበቅን ያዘወተውራሉ። ይህ ደግሞ ልጆች ጨዋታና መዝናናትን ከአባቶቻቸው ብቻ እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል። ይህ በማይሆንበት ጊዜ ልጆች ላይ ድብርትና አንዳንዴም የከፋ የአእምሮ ችግር ያስከትልባቸዋል። ”ምናልባት ጥሩ አባትነት ሲባል ብዙዎች እጅግ ከባድና ብዙ ጊዜ የሚጠይቅ ነገር መስሎ ሊታያቸው ይችላል። ነገር ግን ልጆችን በጉልበታችን ላይ አስቀምጠን አይን አይናቸውን ማየት በራሱ እጅጉን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይችላል። በተለይ ደግሞ አዲስ የተወለዱ ህጻናት ከእናትና አባታቸው ጋር የሚያሳልፏቸው ጊዜያት ወደፊት ማንነታቸውን የመገንባት ትልቅ አቅም አላቸው” ይላሉ ዶክተር ቤከርማንስ ። በልጅ ማሳደግ ሂደት ውስጥ ትልቁ ነገር ጥሩም ይሁን መጥፎ አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ነው። አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ውስጥ ልጆች ቤተሰቦቻቸውን የመላመድና ስሜታቸውን በቀላሉ መግለጽን ይማራሉ። ቤተሰቦች በተለይ ደግሞ ብዙ ጊዜን ከልጆቻቸው ጋር ማሳለፍ የለመዱ አባቶች ልጆቻቸው ምን እንደሚያስደስታቸውና ምን እንደማያስደስታቸው በቀላሉ መለየት ይጀምራሉ። ከዚህም ባለፈ ጥሩና መጥፎ የሚሏቸውን ነገሮች በጨዋታዎች መሃል ለማሳየት እድሉን ይከፍትላቸዋል።

ከልጆች አስተዳደግ ጋር በተያያዘ ባለንበት ዘመናዊ ዓለም ለብዙ አባቶች ችግር እየሆነ ያለው ነገር፤ በሥራ አካባቢና በሌሎች ቦታዎች ስለልጆቻቸው በነጻነት ማውራት አለመቻላቸው ነው። በተቃራኒው እናቶች የፈለጉትን ያክል ስለልጆቻቸው ሁኔታ በሥራ ቦታም ሆነ ከጓደኞቻቸው ጋር ማውራት ይችላሉ። እስቲ ስንቶቹ አባቶች ናቸው ታዳጊ ልጆቻቸውን ወደሥራ ቦታ ይዘው የሚመጡት? ምን ያህሉ አባቶች ናቸው ልጆች ሲታመሙ ወደ ህክምና ቦታ የሚወስዱት? ለእነዚህና ለሌሎች መሰል ጥያቄዎች ያለው ምላሽ “በጣም ጥቂቶቹ” የሚል ነው። ነገር ግን አባቶች ብዙ ጊዜያቸውን ከልጆቻቸው ጋር ማሳለፍና ጨዋታዎችን ማብዛት ሲጀምሩ በየትኛውም ጊዜም ሆነ ቦታ አብረዋቸው ለመሆን ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ ይመጣል ይላል ጥናቱ።