የይቅር ባይነት ሃይል

ቤትዎ አሊያም መሥሪያ ቤትዎ ሆነው ድንገት ደርሶሙድዎ ከተበከለ ቀንዎ ከጨለመ፤ አንድ ነገር ያስተውሉ ይላሉ ሳይንቲስቶች፤ በዙሪያዎ ያለ ድምፅን።

ከቢሮ ሊሆን ይችላል ወይም ከመመገቢያ ሥፍራዎች [ሬስቶራንት] እንዲሁም ሰው ከሚበዛባቸው ቦታዎች የሚወጡ ድምፆች ከመሬት እና ጣራ ጋር ሲጋጩ የሚፈጥሩት ሌላ ዓይነት ድምፅ አለ። በተቃራኒው ወለላቸው በእንጨት የተሠራ ሕንፃዎች ድምፅን የማፈን ባሕርይ ስላላቸው ለአእምራችን ውስጣዊ ሰላም ይለግሳሉ። ድምፅ እንደሚያገኘው ነፃነት ባሕሪው የሚለዋወጥ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረው አይጠግቡም። ሕንፃ ሲገነባ ሰው ወይም ሌላ ቁስ እንዲኖርበት አሊያም እንዲከማችበት ብቻ ሳይሆን፤ ምን ዓይነት ድምፅ ሊያስተናግድ ይችላል የሚለውም ከግምት ውስጥ እንዲገባ የሥነ ሕንፃ ሰዎች ይመክራሉ። ባለሙያዎች ሕንፃን ሲገነቡ ምን ዓይነት ቁስ ነው የሚጠቀሙት ምን ዓይነት ቅርፅስ እንዲኖረውስ ይፈለጋል? ሊዘነጋ የሚገባው ጥያቄ አይደለም።

ትሬቨር ኮክስ የአኩስቲክ ኢንጅነር ናቸው። ብዙ ጊዜ ዙሪያችንን ለማስተዋል ዓይናችንን እንጠቀም እንጂ ጆሯችን ሁሌም አሰሳ ላይ እንደሆነ የሚናገሩት ባለሙያው «ጆሯችን መረጃን ከመልቀም ቦዝኖ አያውቅም» ይላሉ። «ዓይናችን ተሸፍኖ አንድ ወና ቤት ብንገባ በምንሰማው ነገር ብቻ የቤቱን ስፋት፣ የጣራውን ልክ፣ የወለል ንጣፍ ተደርጎለት እንደሁ ማወቅ እንችላለን» የሚሉት ደግሞ ኤሌክትሪካል ኢንጅነር ቤሪ ብለሰር ናቸው። «በጣም በርካታ ነገር ወደ ጆሯችን ይገባል፤ ትኩረት ስለማንሰጠው ነው እንጂ።»

 

የድምፅ ብክለት ምንድነው?

ያልተፈለገ ድምፅ፤ በጉዞ፣ በእንቅልፍ፣ በሥራና ትምህርት፣ በንግግር እና በመሰል የሰው ልጅ የተለመዱ እንቅስቃሴዎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር እና ጤናማ ከባቢን በመበከል በሥነ ልቦናዊ እና አካላዊ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ነው-የድምፅ ብክለት። ሆኖም ግን የድምፅ መጠን እንደ ሰሚው ዕድሜ፣ የጤንነት ሁኔታ፣ እንደ ድምፁ ዓይነት፣ ቆይታና ድግግሞሽ የሚለያይ ነው። ለአንዱ መደበኛ ድምፅ ለሌላው የሚረብሽ፤ ለአንዱ የሚረብሽ ድምፅ ለሌላው ሙዚቃ ሊሆን ይችላል።

ኢትዮጵያ የድምጽ መጠን ለመወሰን መመሪያ አውጥታለች። ሕጉ ለመኖሪያ አካባቢዎች፣ ከንግድ አካባቢዎችና ከኢንዱስትሪ ዞኖች መውጣት የሚገባው የድምጽ መጠን ቀን ቀን 55፣ 65 እና 75 ዲሲቢል እንዲሁም ሌሊት 45፣ 57 እና 70 ዲሲቢል መሆን እንዳለበት በቅደም ተከተል ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን በተለይ አዲስ አበባ የድምፅ ብክለት እጅጉኑ የሚበዛባት ከተማ እንደሆነች ለመናገር መስካሪ አያሻም።

ድምፅ፣ ሙድ እና የአእምሮ ጤና

ድምፅ እና ሕንፃዎች ያላቸው ግንኙት ‘ሙዳችንን’ ሊወስኑት ይችላሉ። ሰዎች መታጠቢያ ቤት ሲገቡ ማንጎራገር የሚወዱት ለምን ይመስልዎታል? ምክንያቱ ድምፃችንን ቅላፄ ይኑረውም አይኑረው ኩልል አድርጎ ስለሚያወጣው ነው። ታድያ ከምንወስደው ‘ሻወር’ ባልተናነሰ ዘና ያለ ስሜት እንዲኖረን ያደርጋል። ኒው ዮርክ ከተማ የሚገኝ አንድ የባቡር ጣቢያ ከምድር በታች የሚገኝ ሲሆን፤ ይህ ከምድር በታች የሚገኝ ሕንፃ ምን ዓይነት ምስጢር መደበቅ አይችልም። ሹክሹክታዎ ሳይቀር ከአንዱ ጥግ ወደ አንዱ ይጓዛል። በተቃራኒው የሚረብሽ ድምፅ ለጭንቀት እንደሚዳርግ፣ ቀናችንን ሊያበላሸው እንደሚችልና በሥራችን ላይ ተፅፅኖ እንደሚኖረው ይነገራል። ጫጫታ በበዛበት፣ ሰው ተጨናንቆ በሚኖርበት አካባቢ መኖር እርዳታ የማጣት ስሜት እንደሚፈጥር፤ በተቃራኒው ድምፅ ባልበዛባቸው አካባቢዎች መኖር ደግሞ ጥልቅ የመመራመር ስሜት እንደሚያጎናፅፍ አንድ ጥናት ያሳያል። ድምፅን ያጠኑ ሰዎች አንዲት ነጠላ ድምፀት [ቶን] ያላት ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው፤ በርካታ ድምፀቶች የሚኖራቸውን ተፅዕኖ ደግሞ አስቡት ይላሉ። ለዚህም ነው ሕንፃ ሲገነቡ ወይም ሲያስገነቡ አሊያም መሥሪያ ቤትዎ ወይም መኖሪያ ቤትዎን ከድምፅ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጢኑበት የሚል ምክር ባለሙያዎቹ የሚሰጡት።