አባል ባለሞያዎቻችን

የኢትዮ ሳይክ አባል ባለሞያዎች

አቶ ወርቅነህ

ቦርድ አባል

ምህረት ደበበ

ቦርድ አባል

ዶክተር ዮናስ

ቦርድ አባል

ዶክተር አቡሽ አያሌው

ቦርድ አባል

ዶክተር ሊያ ከበደ

ቦርድ አባል

አቡ በክር

ቦርድ አባል

ሙሓመድ ሳሊሕ ኑርሁሴን

ቦርድ አባል

ፕሮፌሰር እንድሪያስ

አባል

በተደጋጋሚ የተጠቁ ጥያቄዎች

የኢትዮ ሳይክ አባል ለመሆን የሚያስፈልግ ምንም ቅድመ ሁኔታ የለም። በኢሜይልዎ አልያም በስልክ ቁጥርዎት ራስዎን አባል ማድረግ ይችላሉ።

ጸሃፊው ከሚጽፈው ጽሁፍ ጋር የተገናኘ ወይም ተቀራራቢ ትምህርት አልያም ልምድ ካለው ከድህረ ገፁ ህግጋት የማይፃረሩ ጽሁፎችን ማስገባት ይችላል።

ኢትዮ ሳይክ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ሳይኮሎጂስቶች ማህበር ሙሉ እውቅና ተሰጥቶታል።

የኢትዮ ሳይክ አባል ባለ ሙያዎች በእውቅ ሆስትፒታሎችና ክሊኒኮች የሚሰሩ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚያስተምሩና የተማሩ ብቁ ሙያተኘኞች ናቸው።

ኢትዮ ሳይክ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ያሉትን በጎ ተግባራት በማጉላትና መጥፎዎቹን በማረም ኢትዮጵያ ወደ በጎ ጎዳና የምታደርገውን ጉዞ የበኩሉን ለማገዝ የተገነባ ድህረ ገጽ ነው።

የኢትዮ ሳይክ ትርፍ ከድህረ ገፁ ጠቃሚ መረጃ አግኝተው ሂወታቸው ላይ ያዋሉና ራሳቸውን መለወጥ የቻሉ ግለሰቦች ብቻ ናቸው። 

ለቁሳዊ ትርፍ ያልቆመ

ድህረ ገጹ የሚጠይቀው ገንዘብም ሆነ የሚያስከፍለው ክፍያ የለም። ድህረ ገጹ የተቋቋመው በበጎ ፈቃደኝነት ህዝቡን የሚጠቅም ስራ መስራት ከፈለገ ድርጀት በመሆኑ ራሱን በራሱ ችሎ የሚጓዝ ነው።

ድህረ ገጹ የሚጠይቀው ፤ ምሁራን ያሏቸውን እምቅ እውቀቶች ይዘው ከሚቀበሩ ወደ ህዝቡ ማድረስ የሚችሉባቸውን ፕላት ፎርም በመፍጠር ፤ የተቀረውን ስራ ለህዝብና ለህሊናቸው ማደር በፈለጉ ምሁራን አማካኝነት የሚከናወን ነው።

በበጎ ፈቃደኛ አባላት ስራዎችና ጽሁፎች የተገነባ

ድህረ ገጹ የእውቀት መለዋወጫና መጋሪያ እንደመሆኑ በሁሉም የጽሁፍ ዘርፎች ጽሁፋቸውን ማቅረብ የሚችሉት ፣ ከጻፉት ጽሁፍ ጋር ሙያዊ አልያም ልምዳዊ ግንኙነት ያላቸው ብቻ ናቸው። በመሆኑም ይህ ድህረ ገጽ የአጉል ምሁራን ሳይሆን የእውነተኛ ምሁራን ገጽ ነው። 

ድህረ ገጹ በስነልቦናና ስነባህሪ ፣ በማህበራዊ ሳይኮሎጂና አስተሳሰቦች ፣ በንቃተ ህሊናና በእውቀት ፣ እንዲሁም አጠቃላይ ወደ አብርሆትና እድገት መንገድ የሚመሩ ጽሁፎች መቀመጫ ነው።

ከዘር ፣ ከሃይማኖትና ከፖለቲካ አድልዎዎች የጸዳ

ለአብርሆትና ለንቃተ ህሊና የተቋቋመ ድህረ ገጽ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ፤ ከዘር አልያም ፖለቲካ ፣ አልያም ሃይማኖት ጽሁፎች ሙሉ በሙሉ መጽዳት ይችላል ባይባልም የጽሁፎቹ አላማ ግን አንድን ወገን የወገኑ አልያም አንድን ወገን የጣሉ አይሆኑም።

ሁሉም ሃሳቡን የማራመድና የማሳወቅ መብት አለው። ይህ ድህረ ገጽ ግን ለድጋፍ አልያም ለተቃውሞ ሳይሆን እውቀትን ለመገንባትና ሃሳብ ለመለዋወጥ በመሆኑ ማንኛውም አይነት አድሏዊና መራዥ ጽሁፎች ከድህረ ገጹ ይወገዳሉ።

አባል ይሁኑ

ብርሃን ለተሞላ ነገ ዛሬ ይቀላቀሉን!

የኢትዮ ሳይክ አባል በመሆን ለነገይቱ የበለፀገች ኢትዮጵያ ትውልዳዊ ድርሻዎትን ያበርክቱ።